የዱር ሀብቶችን መጠበቅ ፣ መልሶ መመለስ እና ማጎልበት

ተፈጥሮን መጠበቅ

የተፈጥሮ ሀብታችን ለውጥ የሚወሰነው በመሬት አጠቃቀማችን ነው ©  ክሪስ ሄዋርድ / GWCT
የተፈጥሮ ሀብታችን ለውጥ የሚወሰነው በመሬት አጠቃቀማችን ነው © ክሪስ ሄዋርድ / GWCT

በተፈጥሮ ላይ ያለው ጫና ከፍተኛ ሲሆን ተፈጥሮአዊ ቦታዎችንና ሂደታቸውን መጠበቅና መያዝ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ በቀላሉ ከምህዳሩ ለሚጠፉ ዝርያዎች የመጠለያ ቦታዎች በጣም አስፈላጊ ናችው ምክንያቱም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ለማገገሚያ ከክምችቱ መውስድ ሰለሚቻል፡፡ በአንዳንድ ሞቃታማ ሀገራቶች በሚገኙ ድንግል ቦታዎች የሚገኘው የተፈጥሮ ሀብት በጣም ከፍተኛ ሰለሆነ ገገሚያ ሳያስፈልግ መጠበቅና ማቆየት ይቻላል፡፡ ከነዚህ ውጪ ባሉ ቦታዎች ፍጥረታትንና ስነምህዳራዊ መስተጋብሩን ለመጠበቅ በጣም ጥሩ ነው የሚባለው ጥብቅ የመኖሪያ ቤቶቻቸውን ተፈጥሮዊ በሆኑ መነገዶች ማካለልና ከሌሎች ቦታዎች ጋር ለማገናኘት ተፈጥሮአዊ መሻለኩያዎችን በማበጀት ጥሩ ጥምርታ መፍጠርና እነዲሁም የሰው ልጆችን ጫና መቀነስ ነው፡፡ የተፈጥሮ ማቆያዎች በባህር ውስጥ እንዳለ በብዙ ጫና ምክንያት የተጎዳ ደሴት ከሆኑ ብክለቶችና የውኃ እጥረት ያጋጥማል እንዲሁም ስጋት ላይ ያሉ ፍጥረታቶችን የማቆየት አቅሙ ዝቅተኛ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም የእንስሳ ግቢ ማስፋፋትም ማህበረሰቡ በተፈጥሮ የበለፀጉ ቦታዎች ለመሄድ እና ለመግቢያ ከመክፈል ይልቅ በአካባቢያቸው በሚገኝ ልማትና ጥበቃ ለማስተሳሰር ይረዳል፡፡ በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በዋነኛነት በናሚቢያ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ዝምባቡዌ አብዛኛው በብሄራዊ ፓርኮች ከሚጠበቁት የዱር ህይወቶች ይልቅ ከፓርኮች ውጪ በማደንና በመጎብኘት ጭምር የሚጠበቁት ይበልጣሉ፡፡ ይህ አይነቱ አጠባበቅ ትክክል የሚሆነው ለአንድአንድ ፍጥረታት ይኸውም የአካባቢው ማህበረሰብ በእነርሱ ምክንያት የሚደርሰውን ጉዳት ከአደንና ከሌሎች ከሚያገኙት ጥቅሞች የሚካስ ሲሆን ነው፡፡ የከፈልነው ነው የሚቆየው!

ተፈጥሮን ማደስና ማሻሻል

የባህር ዳርቻ እፅዋትን ወደነበረበት መመለስ ፎቶ © በማርኮ ኩውይሳዳ
የባህር ዳርቻ እፅዋትን ወደነበረበት መመለስ ፎቶ © በማርኮ ኩውይሳዳ

በአለም ዓቀፍ ደረጃ ስኬታማ ከሆንበት 15 በመቶ ከሆነው የመሬት ክፍል ውጪ የሰው ልጆች የሚጠቀሙባቸው የዓለማችን ስነምህዳራዊ መሰተጋብር ጉዳ ከዕለት ወደ ዕለተ እየተባባሰና በሰው ልጆች የምግብና ቁሳዊ ፍላጎቶች ምክንያት በውስጡ የሚገኙትን ፍጥረታቶች ከአካባቢው እየጠፋ ይገኛል፡፡ በእውቀት ላይ ተመስርቶ ከተሰራ ብዙ ጊዜ እንደ መንገድ፣ ግድብ፣ የኃይል ማመንጫዎች እና የንፋስ ኃይል ማመንጫዎች ባሉ መሰረተልማቶች አማካኝነት የሚከሰቱ ችግሮችን መቀነስ ይችላል፡፡ የመኖሪያ ቦታዎች መጥፋትም ከሆነ ችግሩ በመሬት አያያዛችን ላይ ለግብርና፣ ደን ልማት እና ለአትክልት ሰፍራ በሚጠቅም መልኩ ጥቂት ለውጥ ብናደርግ በተፈጥሮ ሀብታችን ላይ ትልቅ አሰተዋፅኦና ለውጥ ልናመጣ እንችላለን፡፡ ለምሳሌ ሰዎች በብዛት በሚኖሩበት አካባቢ ብዘሀ-ህይወትን እነዲኖር የወፍ ጎጆዎችን መስራት፣ በምናለማው የሰብል ማሳችን ውስጥና መብቂያ ላይ ብዘሀህይወትን ለመሳብ ሳሮችን ወይም ሌሎች የተፈጥሮ ዘፎችን መትከል፣ እና መሬትን ከፋፍሎ ለተለያዩ ነገሮችን ማዋል እነዲሁም የተለያዩ እፅዋቶችን መትከልና የመሳሰሉት ጥሩ ተሞክሮዎች ናቸው ተብለው ይጠቀሳሉ፡፡ ይሁን እንጂ ሰዎች በሚኖሩበት አካባቢ ብዘሀ-ህይወትን የበለጠ እነዲኖር ከዚህ የበለጠ ብዙ ስራዎች መሰራትና የመሬት አያያዝን ከመሰረተ ልማት ጋር አጣምሮ ማየቱ ተገቢ ነው፡፡

የዱር ምግቦች ምርት አሰባሰብ ቀድሞ ከነበረው የዘለቄታ ደረጃ የሚለይ ከሆነ በተለይም በማደግ ላይ ባሉ ከተሞች ውስጥ ለገበያ ከሚውለው ሥጋ የሚለይ ከሆነ በዘመናዊ ሳይንስና ባህላዊ ዕውቀት ላይ ተመስርቶ ከማኅበረሰቦች ጋር የጥበቃ እርምጃዎችን መስማማት የግድ ይላል። ለሥነ ምህዳር አስተዳደር ኃላፊነትን ወደ ዝቅተኛ ደረጃ (የስነ-ምህዳር አቀራረብ) ለማስትላለፍ በማይፈልጉ ማህበረሰቦች ምክንያትና ተፈጥሮን አልምቶና ጠብቆ የሰውን ተፅዕኖ ለመካስ መሞከር የልማት ተቃራኒ ነው ብሎ ከማመን የተነሳ ማህበረሰባዊ አቀፍ የተፈጥሮ ጥበቃና ልማት በስፋት እንዳይተገበር አዘግይቶታል። ስለዚህም ምንም እንኳ ተፈጥሮን ተመልሶ እነዲያገግም የማድረግ ስራ በመንግሥታዊ ስትራቴጂ ውስጥ በሰፊው ቢጠቀስም ትግበራ ላይ ግን ደካማ ነው፡፡. መንግሰትና ሌሎች አካላቶችም ከአካባቢው ማህበረሰብና በመሬትና በዱር ዝርያዎች ጥልቅ ፍላጎት ካላቸው ማህበረሰቦች ጋር ተፈጥሮን የማገገም ስራ በጋራ ለመስራት ትብብር ማድረግ አለባቸው። ምክንያቱም የተለያዩ ፍላጎት ያላቸው ማህበረሰቦች ልዩ ሚና ሊኖራቸው ስለሚችል ነው ለምሳሌ የጭልፊት አዳኞች ለወፎች ማረፊያ ምቹ የሆኑ የኃይል-መስመሮች ሲያበረታቱ አዕዋፋት ጎብኚዎች የንፋስ-ሀይል ማመንጫዎችን በጥንቃቄ በተመረጡ ቦታዎች ላይ እነዲተከሉ ይፍልጋሉ፡፡

የከተማ ስነምህዳር

የእፅዋት ብዝሀነት የእንስሳ ብዝሀነትም እነዲኖር ይረዳል © ጄምስሃርት / ሹትርስቶክ
የእፅዋት ብዝሀነት የእንስሳ ብዝሀነትም እነዲኖር ይረዳል © ጄምስሃርት / ሹትርስቶክ

የተፈጥሮ ሀብትን ጠብቆ ማቆየትና እንደገና መገንባት ገጠርን ብቻ ሳይሆን ከተሞችንም ይመለከታል ምክንያቱም ምግብ፣ ነፁህ ውሃ፣ የምንተነፍሰውን ንፁህ አየርና ጥሩ የሆነ የአየር ንብረት ለማግኘት ሁላችንም በተፈጥሮ ላይ ጥገኞች ነን፡፡ የአትክልቶች ስፍራዎች፣ መናፈሻዎችና፣ አረንጉዴ ቦታዎች ሁሉም የተንጣለለ መሬትን ጠቀሜታ ማምጣት አለባቸው ምክንያቱም የምህዳሩ አገልግሎት በየትኛውም አካባቢለሰዎች እና ለሌሎች ሕያዋን ፍጥረታት ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪም በከተማዎች የሚኖሩ ሰዎች በገጠር ለሚኖሩ ማህበረሰብ መልካም ነገር ማበረከት ካስፈለጋቸው ወደ ገጠሩ ስፍራ ተመልሰው በመሄድ ስለተፈጥሮ መረዳት ወይም ማወቅ አለባቸው፡፡