ችግሮችን መፍታት

ልክ የዱር ሃብቶች በጊዜ ሂደት ከሚለወጠው መኖሪያ ቤታቸው  ድንበር እነደሚጠቀሙ ባጠቃላይ ቀላል ፖለቲካዎች ከከረሩት ይሻላሉ © ላውሪ ኮቫነን
ልክ የዱር ሃብቶች በጊዜ ሂደት ከሚለወጠው መኖሪያ ቤታቸው ድንበር እነደሚጠቀሙ ባጠቃላይ ቀላል ፖለቲካዎች ከከረሩት ይሻላሉ © ላውሪ ኮቫነን

ተሞክሮ ዲሞክራሲያው አስተዳደር ከአምባገነናዊ ስርዓት እንደሚሻል እናም ብቁ ያልሆኑ፣ ራሳቸውን የሚወዱ፣ ኪሳቸውን ለመሙላት ታች ላይ የሚሉ ወይም ግጭትን የሚያበረታቱ ፖለቲከኞችን ለማስወገድ ሰዎችን ሊያስተምራቸው ይችላል:: እንዲሁ የተፈጥሮ ሀብትን እንዴት በጥሩ ሁኔታ መጠበቅና መልማት እንዳለበት ሰዎች መማር አለባቸው። እንደማንኛውም ሰብዓዊ ጉዳዮች ሚዛን እና መቻቻል ከአክራሪነት በተሻለ ሊሰሩ ይችላሉ ፡፡ዕፅዋትን በመመገብ እና ተፈጥሮአዊ ፊልሞችን በመመልከት ብቻ ሳይሆን ዛሬ በተወሰነ መልኩ በሰው ልጆች ከተያዘው አብዛኛው መሬት የተፈጥሮ ሀብትን በጥሩ ሁኔታ ማኖር የሚቻለው እንስሳቶች በመኖራቸውና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ እንደነርሱ በመቃረም ስነደሰትና ጥቅማቸውን በስፋት ስናደንቅ ነው፡፡ በተጨማሪም የተፈጥሮን ሀብት ለማስተዳደር ልክ እንደ ሰብል በተመሳሳይ ወቅት እነደማስተዳደር በማህበረሰባዊም ስነምህዳራዊም መንገድ ምን ያህል ውስብስብ ሊሆን እነደሚችል መረዳት አዋቂነት ነው፡፡ የዚህ የሁለትዮሽ አስተዳደር ጥቅም ለመረዳትም በሁሉም ሰፍራ ለሚገኙ ማህበረሰቦች ሃሳቡን ማስፋፋት ያስፈልጋል፡፡

የማይፈለጉ ዝርያዎች

የአውሮፓውያን አዳኞች መንግስትን ለመርዳት መደራጀት ይችላሉ፡፡
የአውሮፓውያን አዳኞች መንግስትን ለመርዳት መደራጀት ይችላሉ፡፡

ዝርያዎች አንድ አንድ ጊዜ በተፈጥሮ ከዚህ በፊት ወዳልተስፋፉበት ስፍራ በምክንያት ወይም በስህተት ይመጣሉ፡፡ እነዚህ ዝርያዎች በፍጥነት የሚስፋፉ ከሆነና ካልተስተዋሉ (ምሳሌ፡ ዕፅዋትን ጨምሮ ውሀ ወለድ ዝርያዎች) ለመቆጣጠር ከባድ ናቸው፡፡ እምቦጭ የጣናንና ሐይቅ እነደጎዳ እነዚህ ዝርያዎች ስነምህዳራዊ መስተጋብሩን የሚጎዱ ከሆነ ማሰወገድ አለብን፡፡ በዚህ ጉዳይ ትልልቅ ባለሙያዎች በውቅያኖስ ሳይንስ ሰልጥነዋል፡፡ የአካባቢው ሰዎችም እነዚህ የሚጎዱ ዝርያዎችን የማጥፋት ስራ ላይ የተሰማሩትን ሊተባበሩ ይችላሉ፡፡ እነዲህ አይነቱ ስራ ለማህበረሰቡ ዘለቄታዊ እነዲሆን ህዝቦች ጥቅሙን በፍጥነት ማየትና የሚወገዱ ዝርያዎች አወጋገዳቸው ጤናማ በሆነ መንገድ መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋቸዋል፡፡

ተህዋስያንና ተባይ መቆጣጠር

አንድ አንድ ጊዜ ተባይን ከምግብ ማከማቻ ማስወገድ ይከብዳል © ቶሮክ/ ሸተርስቶክ፡፡
አንድ አንድ ጊዜ ተባይን ከምግብ ማከማቻ ማስወገድ ይከብዳል © ቶሮክ/ ሸተርስቶክ፡፡

ተመሳሳይ የሆነ የማህበረሰባዊ እክሎች የአዳኞችና ተባዮች አያያዝና ቁጥጥር ላይ ይሰራል፡፡ አንድ አንድ ጊዜ የሰው ልጆች በስነምህዳሩ ውስጥ ሰብሎችን ለመመገብ ወይም የዱር ሕይወትን በዘለቄታዊ መንገድ ለመጠቀም ከሌሎች ዝርያዎች ጋር ሲሻሙ የሰውን ህይወትና ሀብት እንዲሁም የገቢ ምንጫቸውን ጠብቆ ለማቆየት መልካም አስተዳደር ያሰፈልጋል፡፡ በአለም ያሉ ብዙ ማህበረሰቦች ችግር ያለባቸውን ዝርያዎችን በመቻልና እነዲፀኑ የሚያሰችላቸውን በህላዊ ትስስር በማድረግ የተፈጥሮ ሀብትን ለመንከባከብና ለመጠበቅ ባህላዊ መንገዶችን መከተል ቀጥለዋል፡፡ በሌላ ስፍራ በስነምህዳሩ ላይ የሚደረጉ መሻሻሎች አደኑን ካልተቆጣጠርን በስተቀር ሁሉንም ዓይነት ነገሮች ለሚያድኑ/ለሚመገቡ እንስሳቶች ሲያደላ በቁጥር ትንሽ ለሆኑ ታዳኝ ለምሳሌ ጎጆአቸውን በመሬት ላይ ለሚሰሩ ወፎች የመጥፊያ ስጋት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ የሚጎዱ ዝርያዎቹን በማይታገሱ ስፍራዎች ችምር የተመረጠው አስተዳደር በዋነኛነት የሚሰራው አዳኞችና ተባዮችን ማስወገድ ላይ ነው፡፡ አዳኞችና ተባዮችን ለመቀነስ ያሉ አማራጮችም ብዙ ጊዜ እያንዳንዱን እንስሳ ለመጠበቅ ቅድሚያ ከሚሰጡ አካሎች ተቃውሞችን ያስከትላሉ፡፡ በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ማንኛውም አስተዳደር አንድ አንድ ጥበቃዎችን ለማቆየት በጥልቅ ሳይንስና ምርምር ላይ መመስረት ያስፈልጋል ለምሳሌ የእንስሳ ዝርያዎችን ችግር በማያስከትሉበት ስፍራ ለመንከባከብ ያንን በታ በመከለል መስራት፡፡ ሙሉ ለሙሉ ዝርያዎችን ማስወገድ በሽታ አምጪ ተህዋስያን ካልሆኑ በቀር በዘመነው ማህበረሰብ ዘንድ ተቀባይነት የለውም፡፡ ሆኖም ግን በተፈጥሮ ዝርያዎች መስፋፉት ወይም ሆን ተብሎ በድጋሚ ዝርያውን መልቀቅ በድጋሚ መቆጣጠርና መንከባከብ እንዲያስፈልግ ሊያደርግ ይችላል፡፡

ተፈጥሮን ያማከሉ መፍትሄዎች

በደን የተሸፈነ ብዘሃህይወት እና የጎርፍ መከላከያዎች የግንኙነት ማሻሻል © IUCN
በደን የተሸፈነ ብዘሃህይወት እና የጎርፍ መከላከያዎች የግንኙነት ማሻሻል © IUCN

ተፈጥሮን ያማከለ መፍትሄዎች ማለት ለሰው ልጆች ደህንነትና ለብዘሃህይወት ጥቅም ለመስጠት በሚያስችል ሁኔታ የተፈጥሮንና የተሻሻለውን ስነምህዳራዊ መስተጋብር ጠብቆ የሚያቆይ፣ በዘለቄታዊ መነገድ የሚያስተዳደርና የሚያድስ ዘዴ ነው፡፡ ለመሳሌ የረግረጋማ ቦታዎች ስነምህዳራዊ መስተጋብሮችን ማደስ ወጪ በተጎዳ ስነምህዳራዊ መስተጋብር አካባቢ ለንፁህ ውኃ ከምንከፍለው ክፍያ ያነሰ ነው በተለይ ደግሞ የታደሰው ስነምህዳራዊ መስተጋብር ብዙ ጊዜ የመዝናኛ እሴት ጥቅሞቹን ያማክላል፡፡ መፍትሄዎቹ በመጠን ሊለያዩ ይችላል ይኸውም ከትልቅና የረዥም ጊዜ መፍትሄዎች (ለምሳሌ ጎርፍን ለመከላከልና ካርበንን ለማከማቸት ደንን መልሶ ማልማት) እስከ ትንሽና የአጭር ጊዜ መፍትሄዎች (ለመሳሌ አትክልቶችን በሰብል እርሻ አጠገብ በመትከል አዳኝ ነፍሳትን መሳብ ሰብልን የሚያጠፉ ታዳኝ ነፍሳት ይታደናሉ) ናቸው፡፡