ተልእኳችን

ተፈጥሮአዊነት ሰዎች የሚኖሩበት ቦታ የተፈጥሮ ሀብትን እና አገልግሎቶችን ወደነበሩበት እንዲመለሱ እና እንዲቀጥሉ ለማድረግ ነው ፡፡

 

የመሬት ስነምህዳራዊ መሰተጋብርና በውስጥዋ የያዘችው ሀብቶችዋ

የመሬት መንቀጥቀጥ ከአፖሎ 8 በጨረቃ ምህዋር ታየ © ናሳ
የመሬት መንቀጥቀጥ ከአፖሎ 8 በጨረቃ ምህዋር ታየ © ናሳ

መሬትን በተዘረጉ ሁለት እጆቻችሁ መካከል እንደሚገኝ የእግር ስ አስቡት፡፡ ህይወትን ከመሬት በላይ ወይም በታች ደግፎ የሚያቆይልን የላይኛው የመሬት ሽፋን ከጣታችን ጥፍር ይልቅ የሳሳ ነው! ይህ በጣም ስስ የሆነው የላይኛው የመሬት ሽፋን በይዘታቸው ውብና ማራኪ የሆኑ የተለያዩ አትክልቶች፤ እንስሳቶች እና ሌሎች ፍጥረታቶች እነረሱን ሊረዱ ከሚችሉ ነገሮች ይኸውም ውሃ አየር እና አፈር ጋር ይዘዋል፡፡ እኛም የሰው ልጆች የዚህ ስነምህዳራዊ መሰተጋብር (ይኸውም የደኖች፤ ተራሮች፤ ሳሮች፤ በረሃዎች፤ ሐይቆች፤ ወንዞች እና ባህሮች) አካሎች ነን፡፡ በመሆኑም ለመኖር በዚህ የመሬት ስነምህዳራዊ መሰተጋብር ሀብትና ጤና ላይ እነደገፋለን፡፡

በስነምህዳራዊ መሰተጋብር ውስጥ ህይወት ያላቸው ነገሮች

ግሬይ ፓርትሪጅ፣ ለጤናማ እርሻ መሬት ምልክት© ማቴጅ ቪራኒክ
ግሬይ ፓርትሪጅ፣ ለጤናማ እርሻ መሬት ምልክት© ማቴጅ ቪራኒክ

እስቲ አሁን ደግሞ በስነምህዳራዊ መሰተጋብር ውስጥ የሚኖሩ በቁጥር ትንሽ የሆኑ ብዝሀ-ህይወትን (እነርሱም አትክልቶች፤ እንስሳቶች፤ ፈንገሶች ወይም ሌሎች ጥቃቅን ነፍሳቶችን) ከብዙ ምግብና የመኖሪያ ስፍራዎች እነዲሁም ከጥቂት አዳኞች፤ በሽታ፤ ጥገኛ ተህዋስያኖች ወይንም ደግሞ ከሌሎች ገዳይ ከሆኑ ነገሮች ጋር አስበዋቸው፡፡ እነደዚህ አይነቱ ብዘሀ-ህይወት ሊያድግ እንደሚችሉ ምርምሮች ያሳያሉ፡፡ ነገር ግን እራሳቸውን ለማባዛት የሚወስድባቸው ጊዜ እንደየሰውነታቸው መጠን ይለያያል ለምሳሌ ባክቴሪያዎች በደቂቃ እራሳቸውን በእጥፍ ሲያባዙ ነገር ግን እንደ ዝሆን ላሉ ትላልቅ እንስሳ አስርና ከአስር አመታት በላይ ሊፈጅባቸው ይችላል፡፡ በቁጥር ብዙ የሆኑ ትናንሽ እንስሳቶችና አትክልቶች ካሉን ደግሞ በአመት ውስጥ በብዙ ሺህ እጥፍ ሊጨምሩ ይችላሉ፡፡ በመጨረሻም እንደዚህ አይነቱ እድገት በሀብት ውስንነትና በድርቅ አማካኝነት ቁጥሩ ያሽቆለቁላል፡፡ ቢሆንም ብዙ ጊዜ በእድሜ ከፍ ያሉ አትክልቶችና እንስሳቶች በዚህ መልኩ አያድጉም፡፡ የተለያዩ አደጋዎች፤ አዳኝ እና በሽታ ከረሀብ ጋር ተተኪ ህፃናትን በሞት ይቀጥፋሉ፡፡ ጥቂቶች ደግሞ ያረጃሉ፡፡ የአንዱ መሞት የሰውን ልጆች ጨምሮ በምህዳራዊ መሰተጋብር ውስጥ ለሚገኙ ሌሎች በህይወት ላሉ ነገሮች ምግብ ይሰጣል፡፡

በስነምህዳራዊ መሰተጋብር ላይ እኛ የሰው ልጆች የምናሳድረው ተፅዕኖ

ሰዎች በቤታቸው እንስሳትንና እፅዋትን ማላመድ ከመጀመራቸው ከብዙ አመታት በፊት የሰው ልጆች ይኖሩ የነበሩት የዱር እንስሳትን በማደንና እፅዋትን ለቅሞ በመጠቀም ነው፡፡ የበረዶ ዘመንን ተከትሎ ግን ግብርና እየተስፋፋ መጣ፣ ሰዎች በአንድ ስፍራ ተረጋግቶ ለመኖር ለእድገትና ለከተማ መሰፋፋት የሚያስችላቸውን የምግብ አቅርቦት ማምረት ጀመሩ፡፡ የህዝብ ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ በመምጣቱ ብዙ ጉዳቶችን በምህዳራዊ መሰተጋብርና በአየር ንብረት ላይ አስከትሎዋል፡፡ ጫናው ስነምህዳራዊ መሰተጋብሩ ከሚችለው በላይ ሲሆን ስነምህዳሩ የሚሰጠውን አገልግሎት በአግባቡ መስጠት ያቆማል ይህም የሰው ልጆችን የገቢ ምንጫቸውንና ሌሎች የተፈጥሮ ገፅታዎችን ጨምሮ ጉዳት ላይ ይጥላል፡፡ ስነምህዳሩ በአግባቡ ካልተያዘ ተግባራችን በገጠራማ አካባቢዎች የዱር ዝርያዎችን ከመጠን በላይ እነዲያድኑና እነዲለቀሙ፡፡ ያስገድዳቸዋል ከተሞችም ብዙ ምርቶችን ለማምረት በሌሎች ቦታዎች በሚገኙ የእርሻ ቦታዎች መሰረት እናደርጋለን፡፡ በዚህ ዘመናዊው ዓለምም ጥቂት ህዝቦች ብቻ ይህንን ሂደት ሲረዱ ብዙ በከተሞች የሚረቁ ህጎች በገጠራማ አካባቢዎች በሚገኙ ማህበረሰቦች ዘንድ አይታወቁም፡፡ እንዲህ የህዝብ ቁጥር ከፍተኛ በሆነበት በዚህ ጊዜ ደግሞ በሳይንሳዊ ዕውቀት የተደገፈ ዘዴ ካልተጠቀምን በሰተቀር በስነምህዳራዊ መሰተጋብር ላይ እየደረሰ ያለውን አስከፊ ጉዳት ማስወገድ ከባድ ነው፡፡