ተልእኳችን

Naturalliance ሰዎች በሚኖሩበት በማንኛውም ስፍራ የተፈጥሮ ሀብትንና አገልግሎታቸውን ወደነበሩበት እንዲመለሱ እና እንዲቀጥሉ ለማድረግ የሚያግዝ ነው ፡፡

 

የመሬት ስርዓተ-ምህዳርና ሀብቶቹዋ

በአፖሎ 8 ተልዕኮ ወቅት መሬት በጨረቃ ምህዋር ታይቶዋል © ናሳ
በአፖሎ 8 ተልዕኮ ወቅት መሬት በጨረቃ ምህዋር ታይቶዋል © ናሳ

መሬትን በተዘረጉ ሁለት እጆቻችሁ መካከል እንደሚገኝ የእግር ኳስ አስቡት፡፡ ህይወትን ከምድር ወይም ከውሃ በላይ እና በታች ደግፎ የሚያቆይልን ምህዋር ወይም የላይኛው የመሬት ሽፋን ከጣታችን ጥፍር ይልቅ የሳሳ ነው! ይህ በጣም ስስ የሆነው የላይኛው ምህዋር በይዘታቸው ውብና ማራኪ የሆኑ የተለያዩ አትክልቶች፤ እንስሳቶች እና ሌሎች ፍጥረታቶች እነረሱን ሊረዱ ከሚችሉ ነገሮች ይኸውም ውሃ አየር እና አፈር ጋር ይዘዋል፡፡ እኛም የሰው ልጆች የዚህ ስርዓተ-ምህዳሮች (ይኸውም የደኖች፤ ተራሮች፤ ሳሮች፤ በረሃዎች፤ ሐይቆች፤ ወንዞች እና ባህሮች) አካሎች ነን፡፡ በመሆኑም ለመኖር በእንዚህ የመሬት ስርዓተ-ምህዳሮች ውስጥ ያሉ ፍጥረታት ሀብትና ጤና ላይ እነደገፋለን፡፡

በስርዓተ-ምህዳሮች ውስጥ ያሉ ፍጥረታት

ግራጫማ ጅግራ ፣ ለጤናማ እርሻ መሬት ዋና ማሳያ ©  Matej Vranič
ግራጫማ ጅግራ ፣ ለጤናማ እርሻ መሬት ዋና ማሳያ © Matej Vranič

እስቲ አሁን ደግሞ የተትረፈረፈ ምግብ እና መኖሪያ ባለው ስርዓተ-ምህዳር ውስጥ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ተህዋሲያን (ዕፅዋት ፣ እንስሳት ፣ ፈንገሶች ወይም ሌሎች ጥቃቅን ተሕዋስያን) ከጥቂት ወይም ምንም አዳኞች፤ በሽታዎች፤ ጥገኛ ተሕዋስያን ወይም ሌሎች ሊገሉ ከሚችሉ ምክንያቶች ውጪ አስቡት፡፡ እነደነዚህ አይነቱ ፍጥረታት በቀላሉ ሊራቡ እንደሚችሉ ምርምሮች ያሳያሉ፡፡ ነገር ግን እራሳቸውን ለማባዛት የሚወስድባቸው ጊዜ እንደየሰውነታቸው መጠን ይለያያል ለምሳሌ ባክቴሪያዎች በደቂቃ እራሳቸውን በእጥፍ ሲያባዙ እንደ ዝሆን ላሉ ትላልቅ እንስሳ አስርና ከአስር አመታት በላይ ሊፈጅባቸው ይችላል፡፡ በቁጥር ብዙ የሆኑ ትናንሽ እንስሳቶችና አትክልቶች ካሉን ደግሞ በአመት ውስጥ በብዙ ሺህ እጥፍ ሊጨምሩ ይችላሉ፡፡ በመጨረሻም እንደዚህ አይነቱ እድገት በሀብት ውስንነትና በድርቅ አማካኝነት ቁጥራቸው ያሽቆለቁላል፡፡ ቢሆንም ብዙ ጊዜ በእድሜ ከፍ ያሉ አትክልቶችና እንስሳቶች በዚህ መልኩ አያድጉም፡፡ በተለያዩ አደጋዎች፤ አዳኝ ፍጥረታት እና በሽታ ከረሀብ ጋር ተያይዞ በሞት ይቀጠፋሉ፡፡ ጥቂቶች ደግሞ ያረጃሉ፡፡ የአንዱ መሞት የሰውን ልጆች ጨምሮ በስርዓተ-ምህዳር ውስጥ ለሚገኙ ሌሎች በህይወት ላሉ ነገሮች ምግብ ይሰጣል፡፡

የሰው ልጆች በስርዓተ-ምህዳሩ ላይ ያለቸው ተፅዕኖ

ሰዎች በቤታቸው እንስሳትንና እፅዋትን ማላመድ ከመጀመራቸው ከብዙ ሚሊዮን አመታት በፊት የሰው ልጆች ይኖሩ የነበሩት የዱር እንስሳትን በማደንና እፅዋቶችን በመቃረም ነበር፡፡ የበረዶ ዘመንን ተከትሎ ግን ግብርና እየተስፋፋ ሲመጣ፣ ሰዎች በአንድ ስፍራ ተረጋግቶ ለመኖር ለእድገትና ለከተማ መሰፋፋት የሚረዳቸውን የምግብ አቅርቦት ማምረት ጀመሩ፡፡ ተያይዞም የህዝብ ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ በመምጣቱ በስርዓተ-ምህዳሩና በአየር ንብረት ላይ ብዙ ጉዳቶችን ማስከተል ጀመረዋል፡፡ ጫናው ስርዓተ-ምህዳሩ ከሚችለው በላይ ሲሆን ስርዓተ-ምህዳሩ የሚሰጠውን አገልግሎት በአግባቡ መስጠት እያቆመ ይሄዳል በመሆኑም የሰው ልጆችን የገቢ ምንጭና ሌሎች የተፈጥሮ ገፅታዎችን ጨምሮ ጉዳት ላይ መጣል ይጀምራል፡፡ በመሆኑም ስርዓተ-ምህዳሩ በአግባቡ ባለመያዙ ተግብራችን በገጠራማ አካባቢዎች ያሉትን የዱር ዝርያዎችን ከመጠን በላይ እነዲታደኑና እነዲቃረሙ ያስገድዳቸዋል፡፡ከተሞችም ብዙ ምርቶችን ለማምረት በሌሎች ቦታዎች በሚገኙ የእርሻ ቦታዎች ላይ ይመሰረታሉ፡፡ በዘመናዊው ዓለም ውስጥ የተካተቱትን ሂደቶች የሚገነዘቡ ጥቂት ህዝቦች ብቻ ናቸው፣ እና በከተሞች በአብዛኛዎቹ የሚሰጡት ህጎች ብዙውን ጊዜ በገጠር ውስጥ ባሉ ማህበረሰቦች ዘንድ ተቀባይነት የላቸውም፡፡ እንዲህ የሰው ልጅ ቁጥር ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ በሆነበት በዚህ ጊዜ ደግሞ በሳይንሳዊ ዕውቀት የተደገፈ ዘዴ ካልተጠቀምን በሰተቀር በስርዓተ-ምህዳሩ ላይ እየደረሰ ያለውን አስከፊ ጉዳት ማስወገድ ከባድ ነው፡፡